የህክምና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት
- ዳይሬክቶሬቱን ስትራቴጂያዊና ዓመታዊ እቅድ ያቅዳል፣ ይተገብራል፣ ይከታተላል፤ ይገመግማል፤ ወቅታዊ ሪፖርትም ለሚመለከተው አካል ያስተላልፋል፣
- የህክምና መሳሪያዎች በየደረጃው ላሉ ተቋማት እንዲሟላ የሚመለከታቸውን የስራ ክፍሎች ያግዛል፣ይከታተላል፡
- መረጃዎችን በጋራ መጠቀም እንዲቻል በመረጃ ቋት ውስጥ ያስገባል
- የዳይሬክቶሬቱ ተግባራት ሲታቀዱ፣ ሲፈፀሙና ሲገመገሙ አገልግሎት ሰጭዎች ርህሩህና መልካም ስነ-ምግባር በተሞላበት፣ ለተገልጋይ አክብሮት በሚሰጥና በሚንከባከብ አግባብ እንዲፈፅሙ አስፈላጊውን ድጋፍ ይሰጣል፤ ይከታተላል
- የጤና ልማት ሰራዊት አደረጃጀትን በመጠቀምና የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማጠናከር የጤናው ሴክተር ትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች ተግባራዊ እንዲሆኑ ይከታተላል፣ ይደግፋል
- በዳይሬክቶሬቱ ቀጣይነት ያለው ተቋማዊ የአቅም ግንባታ ተግባራትን ይመራል፣ይከታተላል
- በዳይሬክቶሬቱ የባለድርሻ አካላትን የቴክኒክና ፋይናንስ ድጋፍ ያቀናጃል፤ያስተባብራል፤ ይመራል
- ጥናትና ምርምር ያደርጋል፣ያስተባብራል፣ይከታተላል
- መልካም ተሞክሮዎች እና አዳዲስ አሰራሮች ሲኖሩ ለሚመለከታቸው አካላት ተሞክሮዎችን ያስተላልፋል
- የጤና ተቋማት የማበረታቻ ስርዓት ይዘረጋል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፣
- የህብረተሰቡን ንቃተ ጤናና ጤና ተቋም (improving health and health system literacy of the community) ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልቶችን ይነድፋል፣ ያሻሽላል፣ እንዲሰርፅ ያደርጋል፡፡
- ሁሉም ጤና ተቋማት የFM-HACA ደረጃን እንዲያሟሉና የሚጠበቅባቸውን የጤና አገልግሎት እንዲሰጡ ይደግፋል፣ ይከታተላል፣
- የጥራት መለኪያ ስታንዳርዶችን በህክምና አገልግሎት መሽጫ ተቋማት እንዲተገበር ያደርጋል፣ ይደግፋል፣ ይከታተላል
- የደም ልገሳ የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎችን በመስራት ጥራቱ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የደም አቅርቦት እንዲኖር ያስተባብራል፣ ይከታተላል፣
- የዲያግኖስቲክስ አገልግሎቶች ሳይቆራረጡ መሰጠታቸውን ለማረጋጥ የሚያስችል አዳዲስ ቴክኖሎጅዎችን ያስፋፋል፣ የክላስተር ትስስርና የናሙና ቅብብሎሽ ስርአትን ይፈጥራል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል
- የቅድመ ጤና ተቋም የድንገተኛ አደጋ ህክምና አገልግሎት፣ኮማንድ ፖስት ማደራጀትና በተቋማት የድንገተኛ ህክምና (ETAT) እንዲጠናከር ያደርጋል፣ ይከታተላል
- የድንገተኛ ህክምና ክፍል በተቋማቱ ደረጃ መሟላት የሚገባቸውን የህክምና መሳሪያዎች፤ መድሃኒቶች፤ ሌሎች ግባቶች ፣ ፕሮቶኮሎች፣ ማንዋሎችና የምርመራ አገልግሎቶች እንዲደራጁ ድጋፍ ይሰጣል፣ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል
- ተቋማት የጽኑ ህሙማን ህክምና አገልግሎትን በደረጃቸው ልክ እንዲሰጡ ያደርጋል፣ ፕሮቶኮሎችን ያዘጋጃል፣ አቅማቸውን ይገነባል፡፡
- የጤና ክብካቤ ሃብት ማግኛ ሪፎርምን ያስተገብራል፣ ያጠቃቀም ስርዓቱ ያጠናክራል ፣ የሆስፒታል አማራር፤የቦርድ እና የስራ አመራር ኮሚቴዎች ስልጠና ይሰጣል፣ ኦዲት እንዲደረግ ያደርጋል፣ ይከታተላል
- የአገልግሎት ክፍያ ክለሳ ጥናት ያካሂዳል፣ ያሻሽላል፣ በክልሉ መንግሰት እንዲፀድቅ ያደርጋል፣ ሲፈቀድ ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፣ ይከታተላል
- የጤና መድን ፕሮግራሙ ስኬታማ እንዲሆን አባላት የማፍራት፤ የማደስ፤የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱን ከሚመለከተው አካል ጋር ያስተባብራል፣ የሜዲካል ኦዲት ስራ በተጠናከረ ሁኔታ እንዲሰራ ይከታተላል፣ያስተባብራል
- የጤና ጣቢያ ሪፎርምን ያስተገብራል፣ የጤና ተቋማት ጥምረት ለጥራት(EPAQ) የመደጋገፍን ስርዓት ያጠናክራል፣ የሆስፒታል ጤና ጣቢያ ድጋፉ ከወረዳ ጋር በጥምረት እንዲካሄድ ያደርጋል፣ የሆስፒታል ክላስተር የመደጋገፍ ስርአቱን ያጠናክራል፣ ያስተባብራል፣ ይከታተላል
- የጤና አገልግሎት ጥራት ስትራቴጂን ያስተገብራል፣ ይከታተላል፣ ይደግፋል ፣ተግባራዊነቱንም ያረጋግጣል
- አዳዲስ የተቀረፁና የሚቀረጹ የለውጥ ሃሳቦችን (CASH, SaLTs, HSTQ, EHIAQ, EPAQ, EHSTG, Telemedicine, APTs, etc) ያስተገብራል፣ ያስተባብራል