በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት
በዳይረክቶሬቱ የሚተገበሩ ተግባራት፡-
1. የጤና አገልግሎት አሰጣጥና አስተዳደር የማጠናከር፤
2. ለጤና ፕሮግራሞች አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን የማቅረብና ማሟላት፤
3. በጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሞችን የግልና የአካባቢ ንጽህናንና፤ የቤጸብ ጤና ክብካቤንና የተላላፊ በሽታዎች ቁጥጥርን በህብረተሰብ ደረጃ እውን እንዲሆን ሰፊ ርብርብ ማድረግን፤
4.. የጤና ኤክስቴንሽንና የሌሎች ባለሙያዎችን አቅም የመገንባት፤
5. የሴክተሩን እቅድ፤ ክትትልና ድጋፍ ግምገማና ግብረመልስ ማድረግ፤
6. የጤና መረጃ አያያዝንና አጠቃቀምን ማጠናከር፤
7. የኤ.አይ.ቪ/ኤድስ በሽታ ጫና፤ስርጭትና ተጽኖ በመግታት ሂደት በማህበረሰብና በተቋም ደረጃ አቅምና ባለቤትነት የሚያጎለብቱ ማህበረሰብን ማዕከል ያደረጉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት፤ ማለትም የመከላከል፤ የህክምና፤ ድጋፍና እንክብካቤ አገልግሎቶችን የማስፋፋት፤
8. የሰለጠነ የሰው ኃይል ልማትን የማጠናከርና የማሰልጠኛ ተቋማትን የመቀበል አቅም ማሳደግ፤
9. መሰረታዊ የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማትን የማስፋፋትና የማጠናከር ተግባራትን መከታተልና ማስተባበር፤
10. ችግር ፈቺ የጤና ምርምርና ጥናት ማካሄድና ማስረጽ