ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ የሲዳማ ብ/ክ/መ/የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር
የሲዳማ ብ/ክ/መ/የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
Sidaama N/R/S/Public Health Institute
በሲ/ብ/ክ/መ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲቲዩት የሚተገበሩ ዋና ዋና ተግባራት
የክልሉን የጤና አገልግሎት ለማሻሻል፤በክልሉ ውስጥ ያለውን ሰባዊ ሀብት ጤንነት በመጠበቅ ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር በ2013 ዓም በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 11/2013 ዓም ኢኒስቲቲዩቱ ተቋቁሟል፡ ፡
ኢኒስቲቲዩቱ የጤናና ጤና ነክ ችግሮች ላይ ምርምር በማድረግ ፤ በሳይንሳዊ መረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ አሰጣጥን በማሳደግ፤ የቴክኖሎጂ ሽግግር ማድረግ፤ የቅድመ-ዝግጁነት፤ ምላሽ አሰጣጥ፤ ተሀድሶና መቋቋም የሚችል የጤና ስርዓትን በማጠናከር ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎችን መከላከልና መቆጣጠር እንዲሁም ዘመናዊ እና ጥራት ያለው የላብራቶሪ አገልግሎትን ተደራሽ ማድረግ የህብረተሰብ ጤና ልማትን ለማሳደግ እየሰራ ይገኛል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዓላማዎች
- የጤና ምርምር ልማትን ማሻሻል፤
- የህብረተሰብ ጤና አደጋዎችን መከላከል እና ቁጥጥርን ማሻሻል፤
- ጥራቱ የተረጋገጠ የላቦራቶሪ አገልግሎትን ማሻሻል፤
- የጤና አመራር ልማትና አስተዳደርን ማሻሻል
- የጤና መረጃ ክምችት፤ አስተዳደርና ቅመራን ማሻሻል ናቸው፡፡
ኢኒስቲቲዩቱ የጤና ልማት ምርምር፤ የህረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር እንዲሁም በላብራቶሪ እና በጤና መረጃ አስተዳደርና ቅመራ በአራት ዋና ዋና ዳይሬክቶሬቶች ተዋቅራል፡፡ ኢኒስቲቲዩቱ 131 ቋሚና 27 ኮንትራት ሰራተኞች አለው፡፡
ራዕይ
በኢትዮጵያ፣በምስራቅ አፍሪካ በህብረተሰብ ጤና ቀዳሚ የልህቀት ማዕከል መሆን።
ተልዕኮ
በክልል ደረጃ ቅድሚያ በተሰጣቸው የጤና ጉዳዮች ላይ ምርምር ማካሄድ።
የሕብረተሰብ ዋና ዋና የጤና ችግሮችን ለመቅረፍ የቴክኖሎጂ ሽግግርን በመታገዝ ለጤና አገልግሎት ጠቃሚ የሆኑ ግብአቶችን ማምረትና ለሕብረተሰቡ እንዲደርስ ማድረግ።
የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከል ቁጥጥር ፣ቅኝት በማካሄድ ሥጋቶችን ቀደሞ መለየት በቂ ዝግጅት ማደረግ ፣መከላከል፣ ማስጠንቀቅ እና መረጃ ማሰተላለፍ
የኢንስቲትዩቱን ላቦራቶሪዎች በሰለጠኑ ባለሙያዎች እና በላቀ ቴክኖሎጂ ማጠናከር።
ከጤና ጋር የተገናኙ መረጃዎችን ለመሰብሰብ፣ ለማከማቸት እና ለማስተዳደር፣ በማስረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ አሰጣጥን እና የህዝብ ጤና ፖሊሲዎችን እና ፕሮግራሞችን የማሳወቅ ማእከላዊ ስርዓት መዘርጋት።
ግብ
ጤናን በማጎልበት የጤና እርምጃዎችን እና የበሽታ መከላከያዎችን በማስፋፋት ለክልለ ህዝብ ጤናማ ዜጋ ማፍራት.
እሴቶች
በስትራቴጂክ እቅድ መመራት
ውጤታማነት
ለተገልጋይ ክብር መስጠት
ግልጽኝነት
ጊዜ እና ሀብትን በአግባቡ መጠቀም
በውድድር እና በትብብር ላይ የተመሰረተ ጠንካራ የስራ ባህል ማዳበር።
ለተጨማሪ መረጃ የተቋሙን መረጃ ድረግጽ ይጎብኙ፡ https://www.sphi.gov.et/