Skip to main content

 

sec

                                       

        የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

በግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ውስጥ የሚሰሩ ዋና ዋና ስራዎች

  • በየወሩ ስራ ማስኬጃ ገንዘብ፡- ደመወዝ እንዲሁም ካፒታል፣ ወሩ በገባ በ10ኛው ቀን ከፋይናንስ ቢሮ ጠይቆ ማምጣት፤
  • ልዩ ልዩ መደበኛ በጀት፣ ካፒታል፣ ዩኒሴፍ፣ ዋን ዋሽ፣ ጂኲፕ እና ሌሎች እንዲህ አይነት ክፍያዎች መመሪያውና ደንቡ በሚፈቅደው መሰረት መክፈል፤
  • ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ተቀናሽ ግብርና እንደዚሁም ልዩ ልዩ የአደራ ገንዘብ በመሰብሰብ ወሩ በገባ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው በማስተላለፍ ማስረጃ መውሰድ፤
  • ወሩ በገባ በ25ኛው ቀን ለሰራተኞች የሚከፈል ፔይሮል በማዘጋጀት ባንክ በመላክ ከ26ኛው ቀን ጀምሮ አፈጻጸሙን መከታተል፤
  • በየወሩ ተሰብሳቢ ሂሳብ በጊዜ መወርዱን መከታተል፤
  • የበጀት ዝውውር ስራ መከታተልና መመዝገብ፤
  • በየወሩ የሂሳብ ስራዎችን በመከታተል ወሩ በገባ እስከ 10ኛው ቀን የባንክን ሂሳብ መከታተል፤
  • በየእለቱ የሂሳብ ምዝገባ በአይቤከስ ሶፍትዌር በመመዝገብ ከቀኑ 10፡30 እስከ 11፡30 ባለው ጊዜ ውስጥ በማስተካከል የማጣራት ስራ መስራት፤
  • የዜሮ ሚዛን ሪፖርት ወሩ በገባ በ10ኛው ቀን ለክልሉ ፋይናንስ ቢሮ መላክ፤
  • በየወሩ ለኦዲት ስራ መረጃ በማዘጋጀት ሂሳቡ እንዲጣራ በማድረግ ስህተት ቢገኝ አፋጣኝ ማስተካከያ ማድረግ፤
  • ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በጀቱን በአግባቡ መክፈልና ስሌቱን ማውረድ፤
  • አመታዊ እቅድ በማሰባሰብ የግዢ እቅድ  ማዘጋጀትና ከሐምሌ 1-30 ባለው  ጊዜ ውስጥ ለግዢ ኤጀንሲ መላክ፤
  • የግዢ ፍላጎት መሰረት በማድረግ እስፔስፊኬሽን ማዘጋጀት፤
  • የጨረታ ሰነድ ማዘጋጀትና ጨረታውን በአግባቡ ማጠናቀቅ፤
  • የቢሮን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ጥራት ያለው እቃ ገዝቶ ማቅረብ፤
  • የዋጋ ጥናት መረጃ ለሚፈልግ  ማቅረብ፤
  • ለተቋሙ ንብረት መለያ ቁጥር መስጠት፤
  • እቃዎችን በመልካቸው ለመለየት ስርአት ባለውና በጥሩ ሁኔታ መዝግቦ መከታተል፤
  • በሶስተኛው መጨረሻ አመት የንብረት ቆጠራ ማድረግ፤
  • የሚጠገኑና የሚወገዱ እቃዎችን በመለየት በመመሪያው መሰረት ማንሳት፤
  • ወደ ሳጥን የሚገባና የሚወጣ ሂሳብ በመከታተል መዝገቡን በመልኩና በጀቱን በርእሱ ለይቶ መመዝገብ፤
  • በየእለቱ ሳጥኑን ማስቆጠርና አስፈላጊ ሰነዶችን በደንብ መያዝ፤
  • የበጀት አመቱን የሂሳብ ሰነድ በወርና በበጀት ምንጭ ግዢና በሌላ በሌላ የክፍያ ሰነድ ለይቶ በሞዴል 42 መዝግቦ መስጠት ወይም መውሰድ፤
  • የግዢ አጠቃላይ ውል ማዘጋጀት፣ ማጽደቅና መረጃ መተንተን፤
  • የግዢ መረጃ በመልክ መልኩ በመለየት መመዝገብ፣ የግምገማ ውጤት በቦርድ ላይ መለጠፍና ለህዝቡ ይፋ ማድረግ፤
  • ጨረታ የሚከፈትበትን ስነ-ስርአት፣ ንብረት መቁጠርና የተበላሸውን ለይቶ የማስወገድ ስራ የስነ-ስርአት ክፍልና ከውስጥ ኦዲት ጋር በቅንጅት መስራት፤
  • የተቆጠረውን ንብረት መመዝገብ፤
  • ለለውጥ የታሰበውንና የቡድን ስራ ባህል ማሳደግ፤
  • የፈጻሚዎችን አቅም መገንባት፤
  • የልምድ ልውውጥ ማድረግ፤
  • ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ማድረግ፤