Education
Wed, 06/05/2024 - 09:29
በሲዳማበከማመጣጠንዊ መንግስት ጤና ቢሮ በዛሬው ዕለት ለጤና አመራሮችና ለጤና ተቋማት ኃላፊዎች ''ብቁ የጤና አመራር ለላቀ ውጤት እና ጥራት '' በሚል መሪ ቃል ለሶስት ቀናት የሚሰጠው ስልጠና ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ ::
በመድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ አብርሃም ማርሻሎ በንግግራቸው ከሁለት ዓመት በፍት በጤና ሴክተር ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር የሚያያዙ ፣ የግብዓት አቅርቦትና አያያዝ እና መሰል ችግሮች እንደነበሩ ገልጸው የጤና ቢሮው አመራሮች ቆም ብለው የችግሩን ምንጮችና የመፍትሄ አቅጣጫን መቀየስ በመቻላቸው በአሁኑ ጊዜ በሴክተሩ የተሻለ ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል ::
በሽታን በመከላከል እና አክሞ ከማዳን አኳያ ዘላቂ መፍትሔ በሚሆኑ ጉዳዮች ላይ በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን በማንሳት በክልሉ ጤና ቢሮ አማካኝነት ለላቀ ውጤት እንስራ በሚል መሪ ቃል የተጀመሩ ስራዎች ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባውም በማብራራት ስልጠናውም በክልሉ የተጀመረውን የጤናውን ዘርፍ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚረዳ እንደሆነ አንስተዋል።
ኃላፊው ለመጣው ውጤት የድርሻቸውን የተወጡ የሴክተሩን መዋቅሮች አመስግነው አሁንም ግን በሚፈለገው መልኩ በተለይም የመሪነት ሚናቸውን በአግባቡ ከመወጣት አኳያ ጉድለት የሚታይባቸው እንዳሉም ጠቁመው ስልጠናው ጉድለቱን ከመዝጋት አኳያ ጉልህ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይታሰባል ብለዋል።
ከስልጠናው በኋላ ሁሉም መዋቅሮች ሞዴል ቀበሌያትንና ወረዳዎችን ለመፍጠር ርብርብ ሊደረግ እንደሚገባም አቶ አብርሃም አሳስበዋል።
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በበኩላቸው በጤናው ሴክተር ይታዩ የነበሩ የአሠራርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመቅረፍ የአለም ጤና ድርጅት ካወጣቸው ስድስቱ መሠረታዊ ዋልታዎች አኳያ ተፈትሸው ከተለዩ በኋላ ''ለላቀ ውጤት እንስራ '' በሚል መሪ ቃል በተሰራው ሥራ በአሁኑ ጊዜ የተሻለ ውጤት ቢመዘገብም ሁሉንም ጤና ተቋማትን በጤናው ዘርፍ የትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች አተገባበር ከማመጣጠን አኳያ የሚታዩ ጉድለቶችን ለመሙላት በዛሬው ዕለት ''ብቁ የጤና አመራር ለላቀ ውጤትና ጥራት '' በሚል መሪ ቃል ለሚቀጥሉት ሶስት ቀናት ስልጠና እንደሚሰጥ ገልጸው ሰልጣኞቹ በክልሉ በተለዩ በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ የሚሰጠውን ስልጠናውን በአግባቡ መከታተል እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመድረኩ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አክቡር አቶ አብርሃም ማርሻሎ ፣ የክልሉ የብ/ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ አሸናፊ ኤልያስ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት እና የተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች ፣ የዞን አስተዳዳሪዎችና የፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣ የዞን ማህበራዊ ዘርፍ ኃላፊዎች
የወረዳ አስተዳዳሪዎች ፣ ዞኖች ጤና ዴስክ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ፣ የወረዳ ጤና ጽ/ቤት ዋና እና ምክትል ኃላፊዎች ፣ የሁሉም ሆስፒታል እና የጤና ጣቢያ ኃላፊዎችና እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተሳትፈዋል።
በመጨረሻም የስልጠናውን አስፈላጊነት እና ሌሎች የጋራ አጀንዳዎች ዙሪያ ለውይይት መነሻ የሚሆኑ ሰነዶች እየቀረቡ ይገኛል ።