Skip to main content
p5
በሲዳማ ብ/ክ/መ/ጤና ቢሮ በዛሬው ዕለት የወባ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር በሚመለከት ለክልል ሴክተር መ/ቤቶች የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሮች ፣ ለሚዲያ አካላት እና ለሃይማኖት መሪዎች ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። ጤናማ ፣ አምራችና የበለጸገ ህብረተሰብ ለመፍጠር እንቅፋት የሚሆኑ ወባን ጨምሮ ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ስለ መተላለፊያ መንገዶቹና የመከላከያ ስልቶችን ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መፍጠር ቁልፍ ጉዳይ በመሆኑ ለስብሰባው ተሳታፊዎች ይህንኑ በሚመለከት ከዚህ በፍት ከተሠራው በላይ ዘንዲሮ በተቀናጀ መልኩ ሊመራ እንደሚገባ መልዕክት ተላልፏል።