Education
Wed, 06/12/2024 - 16:29
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በምስራቃዊ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የተሰሩ የልማት ስራዎችን እየተመለከቱ ይገኛሉ።ርዕሰ መስተዳድሩ በምልከታው ወቅት እንደገለፁት የክልሉ መንግስት የህዝቡን የመልማት ፍላጎት በተገቢዉ መልኩ ምላሽ ለመስጠት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ የጤና ተቋማት ግንባታዎችንም የጎበኙ በዳኤላ ወረዳ የሚገኝ አዲስ ጤና ጣቢያ ግንባታ የተመለከቱ ሲሆን በቀጣይም በዞኑ የተለያዩ የልማት እንቅስቃሴዎች ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።