በዕለቱ ወደ ክልሉ የመጣው የህክምና ቡድኑ በተለያዩ ህክምና ዘርፍ 6(ስድስት) ስፔሻሊቶችንና ሌሎች ባለሙያዎችን የያዘ ቡድን ሲሆን ፤ ለአንድ ሳምንት ሲዳማ ክልል በለኩ ጠቅላላ ሆስፒታል ለሚገለገሉ ታካሚዎች የተለያዩ ዓይነት የህክምና አገልግሎቶችን እና በሆስፒታል ለሚያገለግሉ ባለሙያች ስልጠናዎችን በመስጠት ቆይታ ያደርጋሉ። የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ፥ የክልሉን የጤና አገልግሎት ፍላጎትን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ እድል የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመው ድርጅቱ ከዚህ በፍት የለኩ ሆስፒታል ግንባታ ወጪ በመሸፈን ለተገልጋይ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ከማድረጉ በተጨማሪ ሆስፒታሉን በየጊዜው የሚደግፍ ቡድን በመላክ እያደረገ ላለው ድጋፍ የላቀ ምስጋናቸውን በመግለጽ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የቡድኑ አባላት በቆይታቸውም ጊዜ ከሚሰጡት የቀዶ ህክምና አገልግሎት ውስጥ ፤ የማህፀን ዕጢ ቀዶ ህክምና፣ የማህፀን ውልቃት ህክምና፣ የማህፀን በር ጫፍና የጡት ካንሰር ምርመራ፣ የእንቅርት ቀዶ ህክምና፣ በማንኛውም አካል ላይ የሚገኝ የዕጢ ቀዶ ህክምና፣ የክንታሮት ህክምና እና የሀሞት ጠጠር ቀዶ ህክምና በዋናነት የሚሰጡ ይሆናል። ልዑካን ቡድኑ ከነፃ ህክምናና ሥልጠና ባሻገር በሆስፒታሉ ውስጥ ለቀዶ ህክምና አገልግሎት የሚውሉ የህክምና ግብዓቶች ድጋፍም አበርክተዋል