Skip to main content
aply
im1
በጤና ዘርፍ የተቀመጡ የጤና ልማት ግቦችን ለማሳካት የጤና ልማት አጋሮች ሚና የላቀ መሆኑን በዛሬው ዕለት የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ እያካሄደ ባለው የጤናው ሴክተር አጋሮች የጋራ የምክክር መድረክ ላይ ተገልጿል፡፡ የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በንግግራቸው የማህበረሰቡን መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የህዝቡን የጤና ችግሮች ለመቅረፍ በሚደረገው ርብርብ እንዲሁም ያጋጠሙ ፈታኝ ሁኔታዎችን በማለፍ ሂደት የጤና ልማት አጋሮች ተሳትፎና ሚና የላቀ እንደሆነ አስታውሰው፤ በተለይም የማህበረሰቡ የጤና ተጠቃሚነት ከተረጋገጠባቸውና ስኬት ከተመዘገበባቸው ፕሮግራሞች ለአብነትም በእናቶ
im2

ህፃናትን ከተለያዩ በሽታዎች በመታደግ፣ ጤናቸው እንዲሻሻልና ሞት እንዲቀንስ ከፍተኛ እገዛ ከሚያደርጉ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ውስጥ ግንባር ቀደም የሆነው የህፃናት አድን ድርጅት/ Save The Children / የጤና መረጃ ስርዓትን ለማቀላጠፍ የሚያግዙ ኮምፒውተሮች፣ፕሪንተሮችና ታብሌቶችን ለሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ በዛሬው ዕለት አስረክቧል። የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ድጋፉን በተረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት የህፃናት አድን ድርጅት/ Save The Children / ለቢሮው ትርጉም ያለውና ወቅቱን የጠበቀ እገዛ በማድረጋቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው ድርጅቱ ከቢሮው ጋር ተቀራርቦ በመስራቱ በተለይም…

Np

በዕለቱ ወደ ክልሉ የመጣው የህክምና ቡድኑ በተለያዩ ህክምና ዘርፍ 6(ስድስት) ስፔሻሊቶችንና ሌሎች ባለሙያዎችን የያዘ ቡድን ሲሆን ፤ ለአንድ ሳምንት ሲዳማ ክልል በለኩ ጠቅላላ ሆስፒታል ለሚገለገሉ ታካሚዎች የተለያዩ ዓይነት የህክምና አገልግሎቶችን እና በሆስፒታል ለሚያገለግሉ ባለሙያች ስልጠናዎችን በመስጠት ቆይታ ያደርጋሉ። የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ፥ የክልሉን የጤና አገልግሎት ፍላጎትን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ እድል የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመው ድርጅቱ ከዚህ በፍት የለኩ ሆስፒታል ግንባታ ወጪ በመሸፈን ለተገልጋይ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ከማድረጉ በተጨማሪ ሆስፒታሉን በየጊዜው…

Np

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ መኮንኖች ማህበር የ2024 ''ምርጥ የጤና ዘርፍ አመራር'' ሽልማት ተሸልመዋል። ክብርት ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ መኮንኖች ማህበርን በምክትል ሥራ አስፈጻሚነት እንድመሩም በማህበሩ በተሰጠዎት ኃላፊነትም የክልሉ ጤና ቢሮው የተሰማውን ደስታ እየገለጸ ፤ የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ላበረከቱት በሳል አመራር እያመሰገነ የማህበረሰብ ጤና አገልግሎት ላበረከተሎት ሽልማት እንኳን ደስ አለዎት ለማለት ይወዳል !!!

news image
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በምስራቃዊ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የተሰሩ የልማት ስራዎችን እየተመለከቱ ይገኛሉ።ርዕሰ መስተዳድሩ በምልከታው ወቅት እንደገለፁት የክልሉ መንግስት የህዝቡን የመልማት ፍላጎት በተገቢዉ መልኩ ምላሽ ለመስጠት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ የጤና ተቋማት ግንባታዎችንም የጎበኙ በዳኤላ ወረዳ የሚገኝ አዲስ ጤና ጣቢያ ግንባታ የተመለከቱ ሲሆን በቀጣይም በዞኑ የተለያዩ የልማት እንቅስቃሴዎች ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
p5
በሲዳማ ብ/ክ/መ/ጤና ቢሮ በዛሬው ዕለት የወባ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር በሚመለከት ለክልል ሴክተር መ/ቤቶች የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሮች ፣ ለሚዲያ አካላት እና ለሃይማኖት መሪዎች ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። ጤናማ ፣ አምራችና የበለጸገ ህብረተሰብ ለመፍጠር እንቅፋት የሚሆኑ ወባን ጨምሮ ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ስለ መተላለፊያ መንገዶቹና የመከላከያ ስልቶችን ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መፍጠር ቁልፍ ጉዳይ በመሆኑ ለስብሰባው ተሳታፊዎች ይህንኑ በሚመለከት ከዚህ በፍት ከተሠራው በላይ ዘንዲሮ በተቀናጀ መልኩ ሊመራ እንደሚገባ መልዕክት ተላልፏል።