ህፃናትን ከተለያዩ በሽታዎች በመታደግ፣ ጤናቸው እንዲሻሻልና ሞት እንዲቀንስ ከፍተኛ እገዛ ከሚያደርጉ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ውስጥ ግንባር ቀደም የሆነው የህፃናት አድን ድርጅት/ Save The Children / የጤና መረጃ ስርዓትን ለማቀላጠፍ የሚያግዙ ኮምፒውተሮች፣ፕሪንተሮችና ታብሌቶችን ለሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ በዛሬው ዕለት አስረክቧል። የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ድጋፉን በተረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት የህፃናት አድን ድርጅት/ Save The Children / ለቢሮው ትርጉም ያለውና ወቅቱን የጠበቀ እገዛ በማድረጋቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው ድርጅቱ ከቢሮው ጋር ተቀራርቦ በመስራቱ በተለይም…
በዕለቱ ወደ ክልሉ የመጣው የህክምና ቡድኑ በተለያዩ ህክምና ዘርፍ 6(ስድስት) ስፔሻሊቶችንና ሌሎች ባለሙያዎችን የያዘ ቡድን ሲሆን ፤ ለአንድ ሳምንት ሲዳማ ክልል በለኩ ጠቅላላ ሆስፒታል ለሚገለገሉ ታካሚዎች የተለያዩ ዓይነት የህክምና አገልግሎቶችን እና በሆስፒታል ለሚያገለግሉ ባለሙያች ስልጠናዎችን በመስጠት ቆይታ ያደርጋሉ። የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ፥ የክልሉን የጤና አገልግሎት ፍላጎትን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ እድል የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመው ድርጅቱ ከዚህ በፍት የለኩ ሆስፒታል ግንባታ ወጪ በመሸፈን ለተገልጋይ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ከማድረጉ በተጨማሪ ሆስፒታሉን በየጊዜው…
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ መኮንኖች ማህበር የ2024 ''ምርጥ የጤና ዘርፍ አመራር'' ሽልማት ተሸልመዋል። ክብርት ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ መኮንኖች ማህበርን በምክትል ሥራ አስፈጻሚነት እንድመሩም በማህበሩ በተሰጠዎት ኃላፊነትም የክልሉ ጤና ቢሮው የተሰማውን ደስታ እየገለጸ ፤ የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ላበረከቱት በሳል አመራር እያመሰገነ የማህበረሰብ ጤና አገልግሎት ላበረከተሎት ሽልማት እንኳን ደስ አለዎት ለማለት ይወዳል !!!