Skip to main content

 

sec

                                                      የኮሙንኬሽንና ሚዲያ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

  • የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የህዝብ ግንኙነትና ጤና ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክቶረት በማህበራዊ አገልግሎት በሚሰጠው ጤና ቢሮ ስር በመደራጀቱ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣ ኘሮግራሞች፣ ዕቅዶች እና አፈፃፀሞች በተመለከተ የመረጃ አገልግሎት በመስጠት፣ መግባባትን በመፍጠርና  የጤና ልማት ሀይሎች የመፈፀም አቅም በማሣደግ አፈጻጸማቸውንም በማስተዋወቅ ጥሩ ግንኙነት መፍጠር በሚያስችል መልኩ የጤና ልማቱን ለማፋጠን የጐላ ሚና ይጫወታል፡፡
  • የህዝብን መረጃ የማግኘት መብት ለማስጠበቅና በጤናው ሴክተር በመከናወን ላይ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ለህብረተሰቡ በማድረስ  ስለጤና ልማት ያለውን ግንዛቤ ከፍ በማድረግ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህም በላይ በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚከናወነውን የጤና ልማት ስራ በቀጣይም በየእርከኑ ከሚገኙ አካላት ጋር በመተባበር መረጃ ወደ ህብረተሰቡ ሊያደርስ የሚገባ ይሆናል፡፡
  •  ከጤና ልማት አኳያ የሚያጋጥሙ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት ቢሮው በአጭር፣ በመካከለኛና በረዥም ጊዜ ሊፈታቸው የያዛቸውን በመለየት እንደየቅደም ተከተላቸው እንዲፈቱ ድጋፍ ማድረግና ስለመፈታታቸው ማረጋገጥ እንዲሁም  የአስተሳሰብ ችግር ባሉባቸው ጉዳዮች ላይ በትክክለኛው አስተሳሰብ እንዲቀየሩ የማድረግ ስራ ይሰራል፡፡
  • በተጨማሪም በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የሚታየውን የአፈጻጸም ውጤታማነት መለያየት ለማጥበብ መልካም ተሞክሮዎችን በመለየት፣ በመሰብሰብ፣ ቀምሮ እንዲስፋፉ በማድረግ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች የሚገኘው ህብረተሰብ ጤናውን ማምረት የሚችልበት ዕውቀት እንዲጨብጥ የማድረግ ተግባር መፈጸም ይጠበቅበታል::