1. የሰዉ ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
•የዳይሬክቶሬቱን ተግባራት ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ ይመራል፣ ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ ይወስናል ይቆጣጠራል፣ የስራ አፈጻጸም ይገመግማል፣ ክፍተቶችን ይለያል፣ ያበቃል፣
• ከዘርፉ ስትራቴጂክ ዕቅድ የተመነዘረ ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣
• የተቋሙን ሠራተኞች መንግሥት በወጣው የምዘና ስርዓት መሠረት በየወቅቱ እንዲመዘኑ ያደርጋል፣ በምዘናው ውጤት መሠረትም ቀጣይ ተግባራትን ያከናውናል፣
• በተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች በሚሰጠው የሥልጣን ውክልና መሠረት በሰው ሃብት ሥራ አመራርና አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣ ወይም የሚሰጡ ውሳኔዎችን ተግባራዊነት ይከታተላል፣
• በመንግሥት ሠራተኞች መመሪያዎችና ደንቦች መሠረት ልዩ ልዩ የቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት፣ ዝውውር፣ የዲስፕሊን፣ የቅሬታ ማስተናገጃና እንዲሁም ሌሎች አግባብነት ያላቸው ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙና ተግባራዊ እንዲሆኑ ይከታተላል፣
• አዲስ ለሚቀጠሩ ሠራተኞች ስለ መንግሥት መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም ተቋሙ ስለተቋቋመበትና ስለሚጠበቅበት ውጤት እንዲሁም ስለ መሥሪያ ቤቱ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች ኃላፊነት የማስተዋወቂያ ስልጠና (`Inducation) እንዲሰጥ በማድረግ ወደ ሥራ እንዲሰማሩ ያደርጋል፣
• የዳይሬክቶሬቱን ወቅታዊ የሥራ አፈጻጸም ለበላይ አካል ሪፖርት ያቀርባል፣