Skip to main content

የሲዳማ  //መንግስት ጤናና ጤና ነክ አገ/// ቁጥጥር  ባለስልጣንን   ሥልጣንና ተግባር ለመደንገግ በወጣዉ ደንብ ቁጥር 10/2013 መሠረት የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡፡    

1. የምግብ፣ የመድኃኒትና  ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥርን ለማስፈጸም  የወጡ ሌሎች ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ተግባራዊ መደረጋቸውን ያረጋግጣል፣ይቆጣጠራል፤

2. ምግብ፣ የመድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥርን ለማስፈጸም የወጡ ሌሎች ሕጎችን፣ ደንቦችና ተግባራዊ ለማድረግ ተቆጣጣሪዎችን ይመድባል፤

3. የምግቦችን ደህንነትና ጥራት፣የመድኃኒቶችን ደኅንነት፣ ፈዋሽነት፣ ጥራትና አግባባዊ አጠቃቀም፣ የጤና ባለሙያዎች የአገልግሎት አሰጣጥና የሙያ ስነ ምግባር፣የሀይጅንና የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ጉድለት እና የጤናና ጤና ነክ ቁጥጥር በሚደረግባቸዉ ተቋማት ላይ የቁጥጥር ሥራዎችን ይሠራል፤

4. አግባብነት ያለው አካል የናርኮቲክና ሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶች አገልግሎት ላይ በሚውሉባቸው ተቋማት ለህሙማን ማዘዝን፣ ማደልን፣ አጠቃቀምን፣መመዝገብንና ሪፖርት ማድረግን  ይቆጣጠራል፣ አለአግባብ መጠቀምን ይከላከላል ፤አጠቃቀምን አስመልክቶ ለፌደራሉ ባለስልጣንና ለሚመለከታቸዉ አካላት ሪፖርት ያደርጋል፤

5. ለመንግስት፣መንግስታዊ ላልሆኑ ጤና ተቋማት፤ለጠቅላላና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ ጤና ኬላዎች፣ ክሊኒኮች፣ የመድኃኒት ችርቻሮ ንግድ ድርጅቶች፣ ሚዲካል ላቦራቶሪዎች፣ዲያግኖስቲክ ኢሜጅንግ፣ የምግብ አገልግሎት  መስጫ ተቋማትና ቁጥጥር የሚደረግባቸዉ ጤና ነክ ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ይሰጣል፣ ያድሳል፣ ያሽጋል፣ ያግዳል፣ ይሰርዛል፤

6. በክልሉ የምግብ፣ የመድኃኒት፣ የአካባቢ ጤና አጠባበቅ፣ የጤና ባለሙያዎች እና የጤናና ጤና ነክ ቁጥጥር የሚደረግባቸዉን ተቋማት በሚመለከት የመረጃ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል፤

7. በምግብ ወይም በመድኃኒት መመረዝ ወይም መበከል ምክንያት ለሚደርስ የሞት፣ የጤንነት መታወክ መንስኤ የሆነውን ንጥረ ነገር ልዩ ልዩ ናሙናዎችን በመውሰድ ወይም በመቀበል ለምርመራ ይልካል፣ ምንነታቸውን ያረጋግጣል፣ በዉጤቱም መሠረት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፤

8 የትምባሆ ዝግጅትን፣ ሽያጭን፣ አጠቃቀምን፣ የሚሸጡ ወይም የሚቸረችሩ ድርጅቶችን ማስተዋወቅን፣ አስተሻሸግንና መለያ አሰጣጥንና አወጋገድን ይቆጣጠራል አስፈላጊዉን እርምጃ ይወስዳል፤

9. በክልሉ ውስጥ የወረርሽኝ በሽታ ሲከሰት አስፈላጊ የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራ መካሄዱን ያረጋግጣል፤ አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፤

10. በክልሉ ዉስጥ የጤና አገልግሎት ስራ ላይ ለሚሰማሩ የጤና ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድ ይሰጣል፣ያድሳል፣ ያግዳል፣ ይሰርዛል፤  የሙያ ስነ-ምግባራቸውን ጠብቀው ስለመስራታቸው እያረጋገጠ  ያድሳል፣ ያግዳል፣ ይሰርዛል፤ 

በፌዴራሉ ባለሥልጣን የሙያ ምዝገባና ፈቃድ ለሚሰጣቸው የጤና ባለሙያዎች፣ ለአማራጭና ተደጋጋፊ ሕክምና ባለሙያዎች የሙያ ፈቃዳቸዉ እንዲታደስ የድጋፍ ደብዳቤ ይሰጣል፤

11. የአገልግሎት ጊዜያቸው ያበቃ ምግቦች፣መድኃኒቶችና ጥሬ ዕቃዎቻቸው በአግባቡ መወገዳቸውን ያረጋግጣል፤

12. ከተለያዩተ ቋማት የሚወጡ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ በሕዝብ ጤና ላይ  ጉዳት የማያስከትል መሆኑን ያረጋግጣል፣ ይቆጣጠራል፣ ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን አሰፈላጊውን ዕርምጃ ይወስዳል፣ በቅንጅት ይሰራል፤

13. ሕገ-ወጥ ምግቦችን፣ መድኃኒቶችንና የጤናአገልግሎቶችን ይቆጣጠራል፣ አስፈላጊ እርምጃዎችንም ይወስዳል፤

14. ለህብረተሰቡ የሚቀርብ የመጠጥ ውኃ የጥራት ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ያረጋግጣል ፤ ለሽያጭ የሚቀርቡ ምግቦች፣ መድኃኒቶችንና የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች በፌደራሉ ባለስልጣን መመዝገባቸውን ይቆጣጠራል፤ ያረጋግጣል፤

15.  በክልል ደረጃ የጤና ነክ ቁጥጥር የሚደረግባቸዉ ተቋማት ተገቢውን የሐይጅንና አካባቢ ጤና አጠባበቅ መስፈርት ማሟላታቸውን ያረጋግጣል፤ ይቆጣጠራል፤ አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፤

16.  ለባህል ህክምና አዋቂዎች የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እና የሙያ ፈቃድ ይሰጣል፤ ይቆጣጠራል፤ በህጉ መሰረት አስፈላጊዉን እርምጃ ይወስዳል፤

17. የሥራ ነክ ጤና አጠባበቅን ይቆጣጠራል፤ አስፈላጊዉን እርምጃ ይወስዳል፤

18. ለሽያጭ የቀረበው ማንኛውም ምግብ፣ መድኃኒት ለሰው ምግብነት ወይም  መድኃኒትነት  የማይስማማ መሆኑ ሲረጋገጥ ወይም በህብረተሰቡ ጤና ላይ ጉዳት እንደሚያስከትል የታመነበትን አደገኛ  ኬሚካል በህግ  መሰረት  ይሰበስባል፤ በአግባቡ መወገዱንም ያረጋግጣል፤

20. ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የመካከለኛ፣ የቅድመ ወይም ድህረ ምረቃ የጤና ተማሪዎች የሚማሩትን ትምህርት በተግባር እንዲለማመዱ ወደ ጤና ተቋማት እንዲሰማሩና በአግባቡ ልምምድ ማድረጋቸውን ይቆጣጠራል፣ ያረጋግጣል፤

21. በክልሉ የሚከናወኑ የምግብ፣ የመድሃኒትና የጤና አገልግሎት የንግድ ማስታወቂያዎች ላይ የቁጥጥር ስራዎችን ይሰራል፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፤

22. የንብረት ባለቤት ይሆናል፣ ውል ይዋዋላል፣ በራሱ ስም ይከሳል ይከሰሳል፤

23. ዓላማውን ለመፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡