የዘርፈ ብዙ ምላሽ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከ/መቆ/ዳይሬክቶሬት ተግባራት
- ተጋላጭነትን ትኩረት ያደረገ፣ የላቀ ውጤት ለማምጣት የሚያስችል ጥምር የኤችአይቪ የመከላከል ኘሮግራሞችን በመተግበር በ2025 95% የሚሆኑ ይበልጥ ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎችን በኤችአይቪ መከላከል ፕሮግራሞች መድረስ ፤
- ተጋላጭ ተኮር የሆነ የኤችአይቪ ምክርና ምርመራ አገልግሎትን በማጠናከር በ2025 95% የሚሆኑ ኤችአይቪ በደማቸው ይገኛል ተብሎ የሚገመቱ ሰዎች ኤችአይቪ ተመርምረው ውጤታቸውን እንዲያውቁ ማድረግና የጸረ-ኤችአይቪ መድሃኒት ማስጀመር፤ጥራት ያለው የፀረ-ኤችአይቪ ህክምና አገልግሎትን አጠናክሮ ማስቀጠል
- የሃብት ማፈላለግ አሰራርን ማሻሻልና ለዘርፈ ብዙ ምላሹ HIV ሜይንስትሪሚንግ ትግበራ የሚውል የሃብት አመዳደብንና እና አጠቃቀምን ማሻሻል
- በመረጃ ላይ የተመሰረተ የውሳኔ አሰጣጥ ስርዓትን ለማሻሻል መረጃ የማመንጨት አቅምንና አጠቃቀምን ማሳደግ፣
- ተጋላጭነትን ትኩረት ያደረገ በትክክለኛ መረጃ ላይ በመመስረት ይበልጥ ተጋላጭ ቦታዎችንና ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎችን መለየት፤ በተለዩ ቦታዎች ላይ በልዩነት የሚታዩ አጋላጭ ባህርያት ላይ ትኩረት አድርጎ የመከላከል ሥራዎች መስራትና ከጤና አገልግሎቶች ጋር በማቆራኘት ተጋላጭነት ቅነሳ ማድረግ
- ከፍተኛ አመራሩ ኤች አይቪን በመከላከል እና በመቆጣጠር ሂደት ላይ ድጋፍ እንዲያደርግ ምቹ ሁኔታ መፍጠር
- መረጃን መሰረት ያደረገ የተፋጠነ የኤች ምላሽ ለመስጠት የመረጃ አጠቃቀም እና ስርጭትን ማሻሻል
- በኤች አይቪ መከላከል ዙሪያ የማህበረሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ ለኤች አይ ቪ ፕሮግራም ምላሽ እንዲሰጡ ማድረግና ባለቤትነትን ማጠናከር ፡፡
- የኤች.አይ.ቪ መከላከልን መቆጣጠር አካታችነትን መሠረት ያደረጉ ማህበራዊ መስተጋብሮች ማለትም፤
- የፆታዊ ጥቃቶችን መከላከል እና መቀነስን ፣
- ሴቶችን የኢኮኖሚ ባለቤትነትን ማጠናከር ፣
- መገለልን እና አድልዎ ማስወገድን ፣
- የህብረተሰቡን፤ኤችአይቪ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች ማህበራትን ጥምረት እና የግል ተቋማትን ተሳትፎ ማጠናከር
- ፖሊሲዎችን ማሻሻል
- ጥራቱን የጠበቀና ቀጣይነት ያለው የኮንዶም አቅርቦት አሰራር ማጠናከር፣ አቅርቦትን ለማሻሻል አጋር ድርጅቶች ጋር መቀናጀት፤በማስተባበርና ከመደበኛ ሜይንስትሪሚንግ በጀት ግዥ በማካሄድ ይሆናል፡፡
- የኮንዶም ፕሮግራምን ለማሻሻል የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል፣
- በትምህርት ቤት የሚገኙ ወጣቶችን በባህሪ ለውጥ ተግባቦት ፕሮግራሞች መድረስ
- በክልልከት/ቤቶችዉጭያሉወጣቶችንኢላማያደረጉኤች.አይ.ቪመከላከልአገልግሎቶችን መስጠት እንዲችሉ የወጣት ማዕከላት ማጠናከር
- ከት/ቤትዉጭያሉወጣቶችንየኤች.አይ.ቪ.መከላከልፕሮግራም
- የኤች.አይ.ቪን የመከላከል መልዕክቶችን የያዘ ብዛት የመረጃና የስርጸት ትምህርት ማቴሪያሎችን በሕትመትና የድምፅ ኦድዮ ማሰራጨት
- ከት/ቤቶች ዉጭ ያሉ ወጣቶች ኤች.አይ.ቪ የመከላከል አገልግሎት የሚዉል ኮንደም ማሰራጫ ጣቢያ ብዛት 32 በመጨመር ኮንደም ለተጠቃምዎች ማሰራጨት
- የሃብት ማፈላለግ አሰራርን ማሻሻልና ለዘርፈ ብዙ ምላሹ ለHIV ሜይንስትሪሚንግ ትግበራ የሚውል የሃብት አመዳደብንና አጠቃቀምን ማሻሻል