Skip to main content

                                                                                   ታሪካዊ ዳራ

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት 2012 . ሐምሌ ወር አስረኛዉ  ክልል ሆኖ የተቋቋመ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ እንደ ክልል ሥራ ከጀመረ ሶስት ዓመት ያህል አስቆጥሯል፡፡ ክልሉን በስተደቡብ ኦሮሚያ ክልል(ጉጂ ዞን) እና ጌዴኦ ዞን፣ በስተሰሜን ኦሮሚያ ክልል(ምዕራብ አርሲ ዞን) በስተምዕራብ የደቡብ ክልል(ወላይታ ዞን) እና በስተምስራቅ የኦሮሚያ ክልል(ምዕራብ አርሲ ዞን) ያዋስኑታል፡፡ የክልሉ የቆዳ ስፋት 7,139.1  ስኩየር ኪሎ ሜትር ይሆናል፡፡ የክልሉ መቀመጫ ሐዋሳ ከተማ ሲሆን ከአዲስ አበባ 275 . ርቀት በስተ ደቡብ አቅጣጫ ይገኛል፡፡፡ክልሉ ለአስተዳደር በሚያመች መልኩ ሐዋሳ ከተማን ጨምሮ  በዉስጡ 31 የገጠር ወረዳዎች፣ 7 የከተማ አስተዳደሮች እና 636 ቀበሌያት (89 የከተማና 547 የገጠር ቀበሌያት) የተዋቀረ ነው፡፡

በክልሉ ሶስት አይነት የአየር ንብረት ያለ ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ 29.3% ቆላማ፣ 55% ወይና ደጋማ እና 15.7% ደጋማነው:: በክልሉ ውስጥ ከፍተኛው ቦታ ከመሬት ወለል በላይ 3300 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኘው የጋራምባ ተራራ ጫፍ ሲሆን ዝቅተኛው ሥፍራ ደግሞ በሎካ አባያ ወረዳ በአባያ ዙሪያ ቀበሌ በአባያ ሃይቅ አካባቢ ከባሕር ወለል በላይ 1200 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል፡፡

የክልሉ ህዝብ ብዛት 2007 ማዕከላዊ ስታትስቲክስ መረጃ መነሻ መሰረት 2016 . 4,748,639 ይገመታል፡፡ ይህም የሃገሪቷን 5% ያህል የህዝብ ብዛት የያዘ ሲሆን በክልሎች ደረጃም 6 ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ አብዛኛው የክልሉ ህዝብ ሰፍሮ የሚገኘው በሁሉም የክልሉ ክፍል ሆኖ በምዕራብ በኩል ከሌላዉ አንፃር አሰፋፈሩ ሲታይ የተራራቀ የህዝብ አሰፋፈር ያለ ሲሆን በክልሉ በአንድ ስኩየር ኪሎ ሜትር በአማካይ 665 ሰዎች ይኖሩበታል፡፡ የክልሉ የህዝብ አሰፋፈር በገጠር በከተማ ሲታይ 79% የሚሆነው በገጠር ሲሆን ቀሪው 21% በከተማ የሚኖር ነው፡፡

2016 በጀት ዓመት ከክልሉ ህዝብ መካከል ሴቶች 2,394,739(50.43%) ወንዶች ደግሞ  2,353,900(49.57%) መሆኑ የሚገመት ሲሆን በመውለድ እድሜ ክልል (15-49 የእድሜ ክልል) ውስጥ የሚገኙ ሴቶች  1,106,433(23.3%) እና ነፍሰጡር የሆኑ እናቶች መጠን 164,303(3.46%) በህይወት የሚወለዱ ህፃናት 164,303(3.46%) እድሜያቸው ከአንድ አመት በታች የሆኑ ህጻናት  151,482(3.19%) ከሁለት ዓመት በታች ህፃናት 246,929(5.2%) ከአምስት ዓመት በታች  740,788(15.6%) እና 15-59 ዕድሜ ክልል የሚገኙ 2,293,593(48.3%) መሆኑን የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ስሌት ያሳያል፡፡

የጤና ተቋማት መረጃ

ባሳለፍናቸው አመታት በጤና አገልግሎት አቅርቦት ህብረተሰቡን ለመድረስ የጤና ተቋማት ግንባታ በከፍተኛ ሁኔታ ተከናውኗል፡፡ በአሁኑ ወቅት በክልሉ ውስጥ 21 የመንግስት ሆስፒታሎች(1 ኮምፕርሄንስፍ እስፔሻላይዝድ፤ 5 አጠቃላይ እና 15 የመጀመሪያ ደረጃ) 136 ጤና አጠባበቅ ጣቢያዎች(132 የመንግስት፤ 2 የፖሊስ እና 2 የመያድ) እና 551 ጤና ኬላዎች ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአሁኑ ወቅት 1 የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና በተለያዩ ወረዳዎች 9 ጤና አጠ/ጣቢያዎች በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኙት ግንባታቸው ሲጠናቀቅ የሆስፒታሎች ብዛት ወደ 22 የጤ//ጣቢያ ብዛት 145 ይደርሳል፡፡ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና የግል ጤና ተቋማት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፉ የሚገኙ ሲሆን በአሁኑ ወቅት 5 ሆስፒታሎች፣ 4 ጤና ጣቢያዎች እና 180 በላይ የተለያዩ ክሊኒኮች አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ ከክልሉ ህዝብ ብዛት አንጻር የጤና ተቋማት ስርጭት በንጽጽር ሲታይ ከተቀመጠው ስታንዳርድ አንጻር ዝቅተኛ መሆኑን ያሳያል፡፡  የመያድና የግል ክሊኒኮች ምንም እንኳን በጤና ተቋማትና ህዝብ ጥምርታ ንፅፅር ውስጥ ባይካተቱም ለህብረተሰቡ ከፍተኛ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ 

የጤና አገልግሎት ሽፋን

የጤና አገልግሎት ለማህበረሰቡ ለማዳረስ ባለፉት አስርት ዓመታት ከፍተኛ ጥረት የተደረገ ሲሆን እስከአሁን ባለዉ የጤና አገልግሎት ሽፋን በጤና ጣቢያ 72.0% በጤና ኬላ 58.0% በመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል 31.9% በአጠቃላይ ሆስፒታል 100% እና በኮምፕርሄንስቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 100% መድረሱን ያሳያል፡፡ በቀጣይ ዓመት በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኙ ጤና ጣቢያዎች ተጠናቀው ስራ ሲጀምሩ የጤና አጠባበቅ ጣቢያ ሽፋኑ ወደ 76.7% ይደርሳል፡፡

የጤና አጠ/ጣቢያዎች ብዛት የተሰላው በኢትዮጵያ ጤና ሰታንዳርድ መሰረት ለአርሶ አደር አከባቢዎች 125000 አርብቶ አደር 115000 ከተማ 140000 ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለአርሶ አደርና ከተማ 1100000 ለአርብቶ አደር 160000 ሆኖ ጤና ኬላዎችን በተመለከተ አርሶ አደርና ከተማ 15000 አርብቶ አደር 13000 መሰረት ተደርጎ ነው፡፡ 

የጤና ባለሙያዎች /HEALTH PROFESSIONALS/

2012 በጀት ዓመት መጨረሻ ላይ የጤና ባለሙያዎች ብዛትን ከህዝብ ብዛት አንጻር በንጽጽር ሲታይ አንድ ሃኪም 19,860 አንድ ጤና መኮንን 3,870 አንድ ሚድዋይፍ 7,198 እንዲሁም አንድ ነርስ 989 ሰዎች መሆኑን ያሳያል፡፡ የነርሶች ብዛት አንድ ነርስ 5,000 ሰዎች እና አንድ ጤና መኮንን 10,000 ሰዎች ከሚለው የአለም ጤና ድርጅት ስታንዳርድ አንጻር ለማሳካት የተቻለ ሲሆን በአንጻሩ የሌሎች ሙያዎች ቁጥር ከስታንዳርዱ በታች መሆኑ ታይቷል፡

  መንግስት የጤና ባለሙያዎችን ቁጥር ለመጨመር የጤና ባለሙያ ማሰልጠኛዎችን በማስፋፋት የቅበላ አቅማቸው እንዲያድግ በማድረጉ ከፍላጎት አንጻር ዕቅዱ ሲነደፍ ከነበረበት መነሻ ከእጥፍ በላይ ማድረስ የተቻለ ቢሆንም በተወሰኑ የጤና ሙያዎች ባለሙያዎችን የማሟላት ቀሪ ስራ እንዳለ ያሳያል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሚታየው የጤና ባለሙያዎች ፍልሰት፣ የስነ ምግባር ችግር እና የክህሎት ክፍተት ለወደፊቱ ብዙ ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ ይሆናል፡፡