Skip to main content

 

                 የስነ-ምግባር  መከታተያ

  1. በተቋሙ መልካም ሥነ ምግባር ለማስፈን በፀረ ሙስና ፖሊሲዎች ህጎች ደንቦችና መመሪያዎች ላይ ለተቋሙ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራዎችን ያከናዉናል
  2. የሙስና ወንጀልና ብልሹ አሠራር መከላከል ስለሚቻልባቸዉ ሁኔታዎች የበላይ ኃላፊዎችን ያማክራል
  3. በተቋሙ ለሙስና ወንጀልና ብልሹ አሰራር ተጋላጭ የሆኑ አሠራሮችን ከኮሚሽኑ ጋር በማጥናት ክፍተቶቹ ሊዘጉ ስለሚችሉበት ሁኔታ የመፊትሔ ሀሳብ ማቅረብ፤ስ ጥናቱ ዉጤት ተግባራዊነት ክትትል ያደርጋል
  4. በተቋሙ ዉስጥ ከባድ የሙስና ወንጀል ተፈጽሞ ወይም ሊፈጸም ይችላል ብሎ በተጠራጠረ ጊዜ ለኮሚሽኑ ወዲያዉኑ ያቀርባል
  5. የተቋሙ ኃለፊዎችና ሠራተኞች ሀብታቸዉን እንዲያስመዘግቡና እንዲያሳወቁ ያደርጋል / የሀብት ምዝገባ በማከናወን ለኮሚሽኑ ያስተላልፋል/
  6. በቅርበት የሚገኙ የሥነ ምግባር መከታተያ መዋቅሮች /አዉታሮች/ጋር በትብብር ይሠራል
  7. በተቋሙ በታችኛዉ መዋቅር የተመደቡት የስነ ምግባር አዉታሮችን ይደግፋል ዕቅድና ሪፖርቸዉን ይከታተላል ይቆጣጠራል ድጋፍና ክትትል ያደርጋል
  8. የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የሥነ ምግባር መመሪያ አግባብነት ካላቸዉ የሥራ ክፍሎች ጋር በመሆን ያዘጋጃል ያጸድቃል፤ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል
  9. በተቋሙ የሠራተኞች ቅጥር ዕድገት፤ዝዉዉር ሥልጠናና  የከፍተኛ ትም.ዕድል የዕቃ ወይም የአገልግሎት ግዥን ወይም ማንኛዉንም ሌላ ዉል በሚመለከት ደንብና መመሪያ ተጥሰዋል ብሎ ሲያምን ለተቋሙ በላይ ኃላፊ ማስተካኪያ እንዲደረግ ከአስተያየት ጋር ሪፖርት ያደርጋል ተግባራዊነቱንም ይከታተላል
  10. በተቋሙ የሥነ ምግባር ጥሰቶችን የሚመለከቱ ጥቆመቀዎችን ተቀብሎ በማጣራት በተቋሙ ደንደብና መመሪያ መሰረት በቀጣይነት መወሰድ ስለሚገባዉ እርምጃ የዉሳኔ ሀሳብ ለሚመለከተዉ አካል ያቀርባል፡፡ የተፈጸመዉ ጥፋት ከባድ የስነ ምግባር ጥሰት ከሆነ ወዲያዉኑ ለኮሚሽኑ ያሳዉቃል
  11. በተቋሙ የሚገኝ ሠራተኛ የሙስና ወንጀልና ብልሹ አሠራር በማጋለጡ ማንኛዉም ተጽዕኖ እንዳይደርስበት ክትትል ያደርጋል፡፡ በሠራተኞች ላይ የብቀላ ተጽዕኖ ተፈጽሞ ከተገኘ ጉዳዩን ለኮሚሽኑ ያሳዉቃል 
  12. በተቋሙ የሥነ ምግባር ጉዳዮች ወይምችግሮች ላይ ሠራተኛዉ ወቅታዊ ዉይይት እንዲያደርግ ለተቋሙ የበላይ ኃላፊ ያሳስባል አፈጻጸሙንም ይከታተላል፡፡
  13. የዉስጥ ወይም የዉጪ ኦዲተሮች እርምጃ እንዲወሰድባቸዉ ወይም እንዲሰተካከሉ ሪፖርት የተደረጉ ጉዳዮች የዲሲፕሊንና የቅሬታ ዉሳኔዎች በትክክል  መተግበራቸዉን ይከታተል
  14. ሙስናንና ብልሹ አሠራርን በመዋጋት ግንባር ቀደም የሆኑ ሠራተኞችን ከኮሚሽኑ በሚወጣ መስፈርት መሠራት መዝግቦ በመያዝ ለማበረታቻ ሽልማት እንዲታጩ ያደርጋል
  15. በበጀት ዓመቱ ስለሚከናወኑ ተግባሮች የሥራ መርሀ ግብርና የበጀት ዕቅድ ለተቋሙ ያቀርባል / ለኮሚሽኑም ያሳዉቃል/