Education
Tue, 01/10/2023 - 02:49
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (ኢሕጤኢ) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ ህብረተሰቡ በአገር አቀፍ ደረጃ ተገቢውን የተመጣጠነ ምግብ ተጠቃሚ ለማድረግ የሁሉም የሚመለከታቸው ሴክተሮች በትብብር መስራታቸው አስፈላጊ መሆኑን አስገነዘቡ። ዶ/ር መሳይ ይህንን የገለፁት ዛሬ በኢሕጤኢ ብሔራዊ መረጃ ፕላትፎርም ለሥነ-ምግብ ((National Information Platform for Nutrition) (NIPN-Ethiopia)) እና በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (ሲሕጤኢ) መካከል ትስስር ለመፍጠር እንዲሁም ስራዎችን ወደ ክልሉ ለማውረድ (ካስኬድ) የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ በተፈራረሙበት የምክክር አውደ ጥናት ላይ ነው።
ዋና ዳይሬክተሩ የመግባቢያ ሰነዱን ከተፈራረሙ በኋላ እንደተናገሩት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚደርሱ የጤና ችግሮችን ለመቅረፍ ብዙ እንደሚጠበቅብን እና ፖሊሲ ለመቅረፅ የሚቅርቡ መረጃዎችን ምንጮችን አስተማማኝነት ለማረጋገጥ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መሰብሰብና መተንተን እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
"NIPN-ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ስር ከሥነ-ምግብ ጋር የተገናኙ የፖሊሲ ጥያቄዎችን በማጠናከርና በመተንተን ጉልህ ሚና እየተጫወተ ሲሆን እንዲሀገር የተቀየሱ የስነ-ምግብ ስትራቴጂዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ለማጠናከር ይረዳል። ስለዚህ የመግባቢያ ሰነዱ በሥነ-ምግብ ላይ ፖሊሲውን እና ስትራቴጂውን የመተግበር አስፈላጊነትን ያጠናክርዋል፣” ብለዋል ዶ/ር መሳይ።
ዋና ዳይሬክተሩ የጤና እና የስነ-ምግብ ፕሮጀክቶችን ወደ ህብረተሰቡ ለማድረስ የክልል ጤና ቢሮዎች እና የህዝብ ጤና ተቋማት ወሳኝ ሚናን አጽንኦት ሰጥተውታል። ለማንኛውም ተመሳሳይ ፕሮጀክት ስኬት የእነዚህ ዘርፎች ተሳትፎ ወሳኝ ነው፣” ሲሉም ጨምረው ተናግረዋል።
"የጤና ፕሮጀክቶችን ስኬት ለማጎልበት NIPN/EPHI ከክልል ጤና ቢሮዎች እና የህዝብ ጤና ተቋማት ጋር በትብብር መስራት አስፈላጊ ነው። ከእነዚህ አካላት ጋር በቅርበት መስራት የአመጋገብ እና የጤና ውጥኖች የታለመላቸው ተጠቃሚዎችን በብቃት እንዲደርሱ ለማድረግ ወሳኝ ነው። በየክልሉ ያሉ የህዝብ ጤና ተቋማትን አቅም በማጎልበት ስራቸውን በጥራትና በብቃት እንዲወጡ ማስቻል የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ኃላፊነት ነው ብለዋል ዶ/ር መሳይ።
የ EPHI ዋና ዳይሬክተር ከሲህጤኢ ጋር የተፈረመው ሁለተኛው የካሳዲንግ ስምምነት ፍሬያማ እንደሚሆን ያላቸውን እምነትና በክልሎች ደረጃ እየተከናወኑ ያሉትን ተግባራት የኢትዮዽያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መደገፉን ይቀጥላል፣" ብለዋል.
የሲሕጤኢ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ በበኩላቸዉ እንደተናገሩት ኢንስቲትዩታቸው በካስኬዲንጉ የተቀመጡትን ዓላማዎች ለማሳካት በትጋት እንደሚሰራ ነው።
"በክልላችን ውስጥ የ NIPNን ተግባራት ለማከናወን ሲሕጤኢ ከብዙ ተወዳዳሪዎች መካከል መመረጡ ለኛ ትልቅ ዕድል ነው። ሲሕጤኢ የሚጠበቀውን ያህል ለመስራት ዝግጁ መሆኑን በድጋሚ ማረጋገጥ እፈልጋለሁ፣” ብለዋል፣ ዶ/ር ዳመነ።
የምክክር አውደ ጥናቱን የከፈቱት ኢሕጤኢ የምግብ ሳይንስና ስነ-ምግብ ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ማስረሻ ተሰማ የNIPN/EPHI ውጥኖችን በመላ ክልሎች ማስፋፋትና ያለውን መተግበር ያለውን ጠቀሜታ ያብራሩ ሲሆን ዶ/ር አረጋሽ ሳሙኤል የ NIPN-ኢትዮጵያ አስተባባሪ ደግሞ የNIPN-ኢትዮጵያን ሚና እና አላማ ገልፀው ፕሮጀክቱ ከሚንቀሳቀሰባቸው ዘጠኝ ሀገሪት ውስጥ በአፈፃፀም ኢትዮዽያ ከመጀመሪያዎች ሦስቱ ውስጥ መሆኗን አስረድተዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘም ዶ/ር ታደሰ ዘርፉ ስለ ፕሮጀክቱ ካስኬዲንጉ ለምን እንዳስፈለገ ጠቅልል ያለ ፅሑፍ አቅርበዋል።
NIPN/EPHI ከዚህ ቀደም ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር ተመሳሳይ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ስራውን በሚጠበቀው መልክ እንዲተገበር ማድረጉ የሚታወስ ነው።