Education
Tue, 01/10/2023 - 02:53
በሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ የአስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታሪኩ ዱካሞ በኢትዮጵያና በአለም አቀፍ ደረጃ ባሉት አስገዳጅና አበረታች የህግ ማዕቀፎች የአካል ጉዳተኞችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነትና አካታችነትን በሚሰሩበት ተቋም ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ እና ተፈፃሚነቱንም በቀጣይ እንደሚከታተሉ ገልጸዋል።
ፍትሀዊና ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለመስጠት የአመራርን አቅም መገንባትና የህግ ማዕቀፎችና ዕቅዶች ተግባራዊነቱን መከታተልና መደገፍ መገምገምና ግብረመልስ መስጠትና የእርምት እርምጃዎችን መውሰድ እንዲሁም ግልፀኝነትና ተጠያቂነትን ማስፈን፤ ከሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላትም ይጠበቃል ሲሉ በአጽንኦት ገልጸዋል።
ሰልጣኞች ከስልጠናውበኋላ እውቀትን፣ ክህሎትንና አመለካከትን መሰረት በማድረግ በግላቸውም ሆነ በተቋማቸው ስለአካል ጉዳተኝነት የዳበረ ግንዛቤ እንዳገኙ እና ተግዳሮቶችን በመቅረፍ ምቹ አሰራርን እንዲዘረጋ የሚመለከታቸው አካላትን ግፊት እንደሚያደርጉ እና ፍትሀዊ የጤና አገልግሎቶችን ማግኘታቸውንም እንደሚከታተሉ በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል።
በመጨረሻም በጤናው ዘርፍ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የመሰረተ ልማት ምቹነትና ለአካል ጉዳተኞች እና የተሀድሶ አገልግሎቶች ተደራሽ ማድረግና በሙሉ ተግባራዊነቱ በቁርጠኝነትና በተጠያቂነት መንፈስ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ መረባረብ እንደሚገባ ከመድረኩ ጥሪ ቀርቧል።
በስልጠናውም ከሶስት አጎራባች አካባቢዎች ከሚገኙ የጤና ተቋማት የተወጣጡ ባለሙያዎች እና ኃላፊዎች ተሳታፊዎች መሆናቸው የሚታወስ ነው።