Skip to main content
news image
በሲዳማ ብ/ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ በዛሬው ዕለት ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት በUNICEF GAVI/CIFF ረጂ አካላት ከአምስት ዓመት በታች የሚገኙ ክትባት ተከትበው የማያውቁ ፣ ክትባት ጀምረው ያቋረጡ ፣ ሥርዓተ ምግብ እና የውልደትና የሞት ምዝገባ አስመልክቶ በስምንት ወረዳዎች በሚተገበረው የተቀናጀ ዕቅድ ዙሪያ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የፕሮግራሙ ማስተዋወቂያ ፕሮግራም ተካሄደ !! በመድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ መንግስት የፕሬዝዳንት ልዩ አማካሪ ክቡር አቶ ተሰማ ዲማ በመክፈቻ ንግግራቸው ፤ ከአንድ ዓመት ወዲህ በክልሉ ጤና ቢሮ ''ለውጤት እንስራ በሚል'' የተጀመረው ኢንሼቲቪ ከዚያ በፍት ሲታዩ የነበሩ የውጤታማነት ችግሮችን በእጅጉ የቀየረ ከመሆኑም በላይ የጤና ቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በሀገር ደረጃ ዕውቅና እንዲያገኙ ያስቻለ እንደሆነ ገልጸዋል። ይህም ለዚህ ሴክተር ትልቅ ዕድል በመሆኑ በቀጣይ ዛሬ በአድስ መልክ በስምንት ወረዳዎች በሚጀመረው ፕሮግራም ዙሪያ አልፎ አልፎ የሚታዩ የክትባት እና በሌሎች የሕጻናት ጤና አገልግሎቶች የጥራት ችግሮችን ለመቅረፍ ሁሉም መዋቅሮች ዕድሉን በአግባቡ ሊጠቀሙበት ይገባል ብለዋል። ኃላፊው አክለውም ጥራቱን የጠበቀ የክትባት አገልግሎት ለዜጎች የማቅረብ ጉዳይ የህጻናትን ሞት ለመቀነስ ካለው ፋይዳ አኳያ ተደራሽ በማድረግ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበው ይህንን ድጋፍ ያደረጉ UNICEF GAVI/CIFF የጤና አጋሮችንም አመስግነዋል። የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በበኩላቸው የህጻናትን ጤና ለማሻሻል በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ በመግለጽ በቢሮአችን በተጀመረው ''ለውጤት/ለላቀ ውጤት እንስራ '' ኢንሼቲቪ ከተጀመረ ወዲህ ትርጉም ባለው ሁኔታ በየደረጃው ባሉት መዋቅሮቻችን አበረታች ውጤቶች እንደተመዘገቡ ጠቁመው ዛሬ ተግባራዊ ለማድረግ በስምንት ወረዳዎች ይፋ የሚደረገው በUNICEF GAVI/CIFF የሚደገፍ ፕሮግራም በቢሮ ደረጃ ሥራዎቻችንን በላቀ ጥራት ለመተግበር የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል። ኃላፊዋ አያይዘውም ከተጠቀሱት የጤና አጋሮች $1.2 ሚሊዮን (የአሜሪካን ዶላሪ) ለሁለት ዓመታት የሚቆይ ድጋፍ እንደተገኘ ጠቁመው ለዚሁ ድጋፍ መያድ ድርጅቶቹን አመስግነው ፤ በየደረጃው የሚገኙ ጤና ተቋማት Zero dose, Drop Out rate , Malnutrition , Birth notification and Registration ላይ ከፍተኛ ለውጥ እንዲመዘገብ የባለድርሻ አካላት ርብርብ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል። የቢሮ ኃላፊዋ አክለው ፕሮግራሙ በጭሬ ፣ በአሮሬሣ ፣ አርቤጎና ፣ ማልጋ ፣ አ/ጩኮ ፣ ቢላቴ ዙሪያ ወረዳዎች እና ፣ በሀዋሣ ከተማና በሃዌላ ቱላ ክ/ከተማ በአጠቃላይ በስምንቱ መዋቅሮች የሚተገበር መሆኑን ጠቁመዋል ። በUNICEF የሲዳማ እና የደቡብ ክልሎች ኃላፊ ወ/ሮ መስከረም ደምሴው በበኩላቸው ፕሮግራሙን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት በጤና ቢሮው የተጀመረውን አድሱን ኢንሼቲቪ የዚሁ ፕሮግራም አካል አድርገው በመጠቀም የላቀ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ በመጠቆም ፤ ኃላፊዋ የተገኘውን ሀብት ለታለመለት ዓላማ ማዋልና ማስተዳደር ይገባልም ብለዋል ። በመድረኩ የፕሬዝዳንቱ ልዩ አማካሪ አቶ ተሰማ ዲማ ፣ የፕሬዝዳንት የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ የሆኑት አቶ ባጥሶ ዌዲሳ ፣ የክልሉ ባለድርሻ ሴክተር ቢሮዎች ተወካዮች ፣ የዞኖች አስተዳዳሪዎችና የማህበራዊ ዘርፍ ኃላፊዎች እና ስምንቱ ፕሮጀክቱ የሚተገበርባቸው ወረዳዎች አስተዳዳሪዎች ፣ የወረዳ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣ የጤና አ/ጣቢያ ዎች ባለሙያዎች ፣ እንዲሁም የጤና ቢሮ ማኔጅመንትና ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተሳትፈዋል ።